Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ቅዱስ ጴጥሮስም በጌታችን በኢየሱስ ክርስችስ ማሰናከያ አምጥቶበት ነበርነገር ግን ተገሠፀ። በመጽሐፍ «ፍሬከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር እትተባበሩ ይልቁንም ግለጡት እንጂ» የተባለው ለዚህ ነው።» ያለው በዚህ ምክንያት ነው። ጌታችን ኢየሱስ ከርስቶስ ደግሞ «የእኔስ መብል የላከኝን ፈቃድ አደርግ ዘንድ ሥራውንም አፈጽም ዘንድ ነው። የነፍስ ጌጧ ግን ገድል ምግባርና ትሩፋት ነው። ነፍስ እጅግ ያማረ ሸማ ትለብሳለች እርሱም የቅዱሳን ጽድቃቸው ነው። ይህን በመሰለ መንፈላዊ ሕይወት የተመሳለስን እንደሆነ የንስሐ ሕይወታችንን ከፈተና እንጠብቃለን ወደኋላም ተመልሰን የተውነውን ኃጢአት እንሠራም። ይህ ጽኑ መሠረትም የእግዚአብሔር ቃል ነው። ነፍሳቸውን ዘወትርያእግዚአብሔርን ቃል የሚመግቡ ስዎች ዙሪያዋ በግንብ እንደታጠረ ከተማ ጸንተው ይኖራሉ ፍጹሙ ንስሐ እንግዲህ በእግዚአብሔር ፍቅር ላይ የተመሠረፋና ከኣርሉ ጋር የሚያገናኝ ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎልም «ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም» ያለው ሰዚህ ነው።
ምክንያቱም የሚመጣውን ፈተና ለመቋቋም የሚያስችለው የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችን ነውፍእርሱም ከሥላሴ በተወለድን ጊዜ የተሰጠን ጸጋ መንፈስ ቅዱስ በመሆኑ በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት የመጣብንን መበናክል ልንወጣው ይገባናል። ለኃጢአት ጊዜ አለመስጠት ሰው ለኃጢአት ጊዜ ከመስጠት የተነሣ ደጋግሞ ይወድቃል። ኃጢአትን በመታገሥ ጊዜ የሚሰጠው ሰው ሳያስተውለውና ላያውቀው ቀስበቀስ ወደ ውድቀት እንደሚደርስ ዐውቀን ራሳችንን ከፋት ማዳን ይገባል ኃዉኣትም ጊዜ መስጠትን ከእኛ ልናርቀው ያስፈልጋል። ልባችን ከእግዚአብሔር የራቀ እንደሆነ በእኛና በእርሱ መካከል እንቅፋት የሆነ ፈቃደ ሰይጣን ኃጢአት ይገባል በልባችንም ያለውን ፍቅረ እግዚአብሔር ይከፍልብናል ይቀንስብናል ከእግዚአብሔር የበለጠም ኃጢአትን እንድንወድ ያደርገናል ከአምላካችንም ያጣላናል። ፈሪሃ እግዚአብሔር ከሌለን በፍቅረ እግዚአብሔር ልንኖር አንችልም ፍቅረ እግዚአብሔር በእኛ ዘንድ ከሌለ የእግዚአብሔር መንፈስ ሊያድርብን አይችልም። የዓለም ፍላጎት በመንፈላዊ ሕይወታችን ላይ ተጽእኖ በሚያደርግብን ጊዜ ሁሉ መንፈላዊ በሆነው መሣሪያ በጸምና በጸሎት በመጠቀም ልንዋጋው ይገባል የዚህ መንፈላዊ ውጊያ ውጤት ደግሞ የእግዚአብሔር ፍቅር በውስጣችን ጥልቅ እንዲሆን የረዳናል። ይህን ፍቅር ያጣ ልቡና ግድየለሽ ከመሆኑ የተነሣ ቀድሞ የእግዚአብሔርን ፍቅር ባወቀበት ጊዜ በልቡናው የተቀጣጠለውን ፍጹም መንፈላዊነት ያጣል እናም ይህ ግድየለሽነቱ ወደ ኃጢአት ያድጋል። በልቡናችን ውስጥ የእግዚአብሔር ፍቅር ከሌለ ንስሐ ልንገባ አንችልም። ማንኛውም ነገር በፍቅረ እግዚአብሔር ላይ ተመሥርቶ ካልተደረገ ልማድ እንጂ መንፈሳዊ ሕይወት ነው ሊባል አይችልም። ምክንያቱም ልቡናችንን ፍጹም በሆነ የንስሐ ሕይወት ሊያኖረንና ከእግዚአብሔር ጋር ሊያስታርቀን የሚችለው ፍቅር በልቡናችን ውስጥ ስለሌለ ነው። በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በንስሐ ሕይወት ያልኖርን እንደሆነ መጥፋታችን አይቀርም። እንዲህ ያለ በፍቅረ እግዚአብሔር ላይ የተመሠረተ የቅንነትና የየዋህነት ስሚት ያለው ሰው ያለምንም ችግር ንስሐ ሊገባ ይችላል። በልቡናውፍቅረ እግዚአብሔር ለሌለው ሰው ንስሐ መግባት ከባድ ሸክምና አስቸጋሪው ነው ምክንያቱም የኃጢአትን ፍቅር ገና ከልቡ ጠርጎ አላስወገደምና። ስለዚህ የንስሐ ሕይወታችንን አስቸጋሪ የሚያደርገውን የኃጢአት ፍቅር ከልቡናችን የሚያስወግደውን የእግዚአብሔርን ፍቅር ገንዘብ ማድረግ ይኖርብናል። ንስሐመግባት የተራራ ያህል ገዝፎ የገደል ያህል አስቸጋሪ ሆኖ የታየን እንደሆነ በልቡናችን ያለው የእግዚአብሔር ፍቅር ፍጹም ኣይደለም ወይም ደግሞ ምንም ፍቅረ እግዚአብሔር የለንም ማለት ነው። ኃጢአትን ከጠላን ደግሞ ንስሐን እንወዳለን እርሱም የልብ ንጽሕናን ለማግኘት ያበቃናል» የእግዚአብሔር ፍቅር በልቡናችን ያለውንየኃጢአት ፍቅር አውጥቶ እንደሚጥልልን ስንገነዘብ እንዴት አድርገን ወደ ፍቅረ እግዚአብሔር ልንደርስ እንደምንችል እንጨነቅ ይሆናል። ይህን የሚያብራሩልን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እግዚአብሔር «ሁል ጊዜ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስው በመሆኑና ስለእኛ በመስቀል ላይ በመሞቱ ድል መንሣትን ይስጠናል። ብዙ ጊዜ በመደጋገም የእግዚአብሔርን ዕርዳታ ለማግኘት ጸልየን ንስሐ ለመግባት አልቻልን ይሆናል። ስለሠራው ኃጢአት የሚያለቅስ ከሆነ ደግሞ ንስሐ ለመግባት አይቸገርም ፅንባ ራሱ የንስሐ ምልከት ነውና። እንዲህ ዓይነቱ ተነሳሒ በራሱ ላይ ያዝናል ቅዱስ ይስሐቅም «ስለሠራው ኃጢአት እያሰበ በየቀኑ በሠራው ሥራ የማያዝን ተነሳሒ ምንም እንኳ በዚያ ጊዜ መልካም ሥራዎችንም ቢሠራ አነዚያን በኃጢአት የኖረባቸውን ቀናት እንደአጣቸው ማወቅ አለበት። ስው ሁል ጊዜ ኃጢአቱን የሚያስብ ከሆነ በሠራው መልካመ ሥራ ራሱን ከፍ ከፍ ሊያደርግ አይገኝም። በሠራው ኃጢአት የማያዝን ሰው ንስሐ ገብቻለሁ ሊል አይችልም ራሱን አያውቅምና። ስለኃጢአቱ የሚያስብ ስው እኔ ብዙ ጊዜ በኃጢአት ወድቄአለሁናኛ ሌላው ሰው ከአኔ የተሻለ ቅዱስ ነው ይላል። ቅዱስ ዮሐንስ የተባለ የቤተ ከርስቲያን አባት ማንንም በኃጢአት ያየ አንደሆነ«ስይጣን ዛሬ ወንድሜን ከጣለው ነገእኔን ይጥለኛል ወንድሜን ጌታ ይቅር ብሎት ንስሐ ይገባ ይሆናል እኔ ግን ንስሐ የምገባ ለው አይደለሁም» እያለ አምርሮ ከልቡ ያለቅሳል» ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም «ከእነርሱ ጋር እንደ ታሠረ ሆናችሁ እሥሮችን አስቡ» በማለት የተናገረው ቃል ንስሐ የገባ ስው ንስሐ አንዳልገባ ራሱን በመቁጠር በኃጢአት ላሉት ማሰብና ማዘን የሚገባው መሆኑን ያመለከታል። ተነሳሒ ልቡና ያለውና ሕይወቱን በንስሐ የሚመራ ሰው ለእርሱ አደገኛ አንኳ ቢሆን ስለሴላው ሰው ኃጢአት አይናገርም። ሰዚህም ነው ንስሐ በሚገቡ ስዎች ሕይወት ውስጥ ብዙ ጊዜ መንፈሳዊ ጥንካሬን የምናየው። ንስሐ በልቡናችን ውስጥ ክፍተኛ የሆነ ፍቅረ እግዚአብሔር አንዲወለድ ያደርጋል። እግዚአብሔር የበዛ ኃጢአቱን ይቅር ያለው ሰው የተደረገለትን ይቅርታ እያሰበ በልቡ የ የእግዚእብሔር ፍቅር እየጨመረ ይሄዳል። በኃጢአት በነበረ ጊዜ ከሰይጣን ጋር በነበረው ውጊያ ደካማ ነበር ንስሐ ሲገባ ግን የተለየ ጸጋና መንፈሳዊ ኃይል ያገኛል። ከፍል እምስት የልብንጽሕና ፍጹም ንስሐ ኃጢአትን ጨርሶ መጥላት ልብንም ፈጽሞ ከኃጢአት ማጥራት ሲሆን የልብ ንጽሕና ደግሞ ከፍጹም የንስሐ ምልከቶች አንዱ ነው። ስለዚህ ይህ ለው የንስሐ እርምጃውን ማጠናከር አለበት በናቃቸው ኃጢአቶች ሁሉ ላይ ንስሐ መግባት አለበት በንስሐ ይኖራል ለማለት የሚቻለውም በእርሱ ሃሳብ ጥቃቅን ከሚመስሉት ጀምሮ ኃጢአትን ሁሉ ሲተውና ከልቡናው ፈጽሞ ያጠፋው እንደሆነ ነው። ይህ ሰይጣን ከሰውየው ገለል ብሎ የቆየበት ጊዜ ኃጢአትን የማሸነፍያ ጊዜ አይደለም ጦርነት የሌለበት ጊዜ ነው። ስለዚህ አንድሰው በተወሰነ ኃጢአት ተፈትኖ ራሱን ከዚህ ኃጢአት ቢያነጻ ይህ ፍጹም ንጽሕና ነው ለማለት አይቻልም። ከዚህም የተነሣ መንፈሳዊ የሆነውን ነገር ለመሥራት ጊዜ ያጣል። የልብ ንጽሕና ግንበፍጹም ልብ በፍጹም ሃሳብ በሥራም ያለማዳረጥ ከእግዚአብሔር ጋርባሚሰማማ ሕይወት መኖር ነው። ያን ጊዜ በአኦምሮአችን የተቀረጸውን ሃሳብ ሥፍራ ለንሰጠውና ላናተኩርበት ያሳለፍነው እንደሆነ ይህ የልብ ንጽሕና ቅድመ ሁኔታ ሊፈጥር ይችላል ወይም ደግሞ አእምሮእችንን ያስገዛንለትና ጊዜ የሰጠነው እንደሆነ የኃጢአትን ፍላጎት በውስጣችን ሊፈጥር ይችላል ይህ ሃሳብ በእግዚአብሔር ሰው ልቡና ውሰጥ የኃጢአትን ፍላጎት ሳይሆን በልቡናው ውሰጥ ለኃጢአትና ለዓለም ነገር በመምሞት ላይ እንዲያተኩር የሚያነሣሣ ሃሳብ ሊፈጥርበትይችላል። የእግዚአብሔር ፍቅር ባደረበት በዚህ ሰው ሕይወት ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች በግልጽ ይታያሉ። ይህ ስው ይህን የመፍረድና የመተቸት ኃጢአት እየፈጸመ ከኖረ ከረጅም ጊዜበኋላ ወደ ንስሐ ሕይወት ይገባል። ይህ ሰው ንስሐ ከገባ በኋላ ሊለቀስበት የሚገባ ኃጢኣት በእርሱ ሕይወት ውስጥ መኖሩን በማስተዋል ራሱን ከዚህ ከማንጻት ይልቅ ዓይኖቹ የሌሎች ስዎችን ኃጢአት ለማየት የተከፈቱ ስለሆኑ ስዎችን ሲተችና በእነርሱም ሲፈርድ ይኖራል። በኋላም ንስሐ ገብቶ ወይም ንስሐ እንደገባ በማሰብ ከእግዚአብሔር ጋር በአዲስ ሕይወት ይኖራል። ንስሐ የገባው ሰው ግን የዓለም የሆነውን ነገር ፈጽሞ ከራሱ መለየት አለበት።